በደቡብ ሱዳን የወርቅ ማዕድን ማውጫ በደረሰ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ተገደሉ

በደቡብ ሱዳን በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ቦታ ላይ በደረሰ አሰቃቂ ጥቃት ቢያንስ 73 ሰዎች መገደላቸዉ ተሰምቷል፡፡

ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የተፈጸመው ጥቃት ከዋና ከተማዋ ጁባ በስተደቡብ ምዕራብ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የኮር ካልታን የማዕድን አካባቢን ኢላማ ያደረገ ነበር።

እንደ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄምስ ዋኒ ኢጋ ገለጻ፤ቢያንስ ሌሎች 25 ሰዎች በጽኑ ቆስለዋል።

ኢጋ በሰጡት መግለጫ፤ ለቆሰሉት አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ እንዲደረግ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ በጥቃቱ ላይ ምርመራ እንዲደረግም አቅደዋል።

ባለሥልጣናት ለጥቃቱ ተጠያቂ የሆኑትን አካላት መለየትና የጥቃቱን ዓላማ ማወቅ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ጥቃቱን የፈጸሙት አካላት እስካሁን በውል ያልታወቁ ሲሆን፤እርስ በእርሱ የሚጋጩ መረጃዎች እየወጡ ነው።

አንድ የጸጥታ ምንጭ ከሪክ ማቻር ጋር ግንኙነት ያላቸው ኃይሎች በጥቃቱ ውስጥ እጃቸው እንዳለበት ቢጠቁምም፤የእርሳቸው ተወካዮች ግን ድርጊቱን በመካድ ይልቁንም ለፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ታማኝ የሆነውን ጦር ወንጅለዋል።

ደቡብ ሱዳን በ2011 ነፃነቷን ካገኘች በኋላ በአብዛኛው በፖለቲካዊ ሽኩቻዎችና በትጥቅ ታጋይ ቡድኖች ሳቢያ የሚቀሰቀሱ ተደጋጋሚ የግጭት አዙሪቶች ገጥመዋታል።

የቅርብ ጊዜው ጥቃት የአገሪቱን ደካማ የጸጥታ ሁኔታና በሲቪሎች ላይ የተጋረጠውን አደጋ የሚያጎላ ሲሆን፤ በተለይም እንደ ወርቅ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን ለመቆጣጠር የሚደረገው ፉክክር ግጭቶችን በሚያባብስባቸው ራቅ ባሉ አካባቢዎች ያለውን ስጋት አጉልቶ ያሳያል መባሉን አፍሪካ ኒዉስ ዘግቧል።

ሊዲያ ደሳለኝ

መጋቢት 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *