ማጓዬር የኮንትራት ማራዘሚያ ፈረመ

የማንቸስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ሃሪ ማጓዬር በማንቸስተር ዩናይትድ ለተጨማሪ አንድ ዓመት የሚያቆየውን ኮንትራት ተፈራርሟል፡፡

የተከላካዩ የቀድሞ ኮንትራት በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ ይጠናቀቅ ነበር፡፡

የ33 ዓመቱ ተከላካይ  ሩበን አሞሪም ከማንቸስተር ዩናይትድ ተሰናብተው ማይክል ካሪክ ሃላፊነቱን ከተረከበ ወዲህ ከማንቸስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ አሰላለፍ ከማይጠፉ ተጫዋቾች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የቀድሞው የማንቸስተር አምበል ለማንቸስተር ዩናይትድ 266 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡

ማጓዬር ሌስተር ሲቲን ለቅቆ ማንቸስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው በ80 ሚ.ፓ የዝውውር ክፍያ በ2019 እንደነበር ይታወሳል፡፡

አቤል ጀቤሳ

መጋቢት 29/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *