ሩቢዮ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ጋር ለመገናኘት ቫቲካን ገቡ

በሊቀ ጳጳሱ እና በሩቢዮ መካከል የሚደረገው ዝግ ስብሰባ ለግማሽ ሰዓት ይቆያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከቫቲካን እና ከጣሊያን ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት ሮም ገብተዋል።

በጳጳሱ እና በሩቢዮ መካከል የሚደረገው ዝግ ስብሰባ ለግማሽ ሰዓት ያህል ይቆያል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ሩቢዮ ከስብሰባው በኋላ ከቫቲካን ከፍተኛ ዲፕሎማት ከጣሊያናዊው ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ጋር ይገናኛሉ።

ሩቢዮ አርብ ዕለት ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጉብኝቱ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ እና በቫቲካን መካከል በዓለም አቀፍ ደህንነት እና ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እየተደረገ ባለው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የተገኘ ነው።

ስብሰባው የተካሄደው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጳጳሱ ‹‹ለብዙ ካቶሊኮች አደጋ እየፈጠሩ ነው››ሲሉ ከወነጀሉ በኋላ ነው።

ትራምፕ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ጳጳሱ ‹‹ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንዲኖራት ይፈቅዳሉ›› ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ አስተያየት በኋይት ሀውስ እና በቫቲካን መካከል ያለውን ውጥረት ይበልጥ እንዲባባስ አድርጎታል።

ይህም ጳጳሱ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ በሚያደርጉት ጦርነት ላይ ከሰነዘሩት ቀደምት ትችት በኋላ የመጣ ነው።

እስከዳር ግርማ

ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *