የብቃት መመዘኛውን በዲጂታል ሥርዓት ለማከናወን የሚያስችል አዲስ መተግበሪያ ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ተሳስሮ የተዘጋጀው ይህ ሲስተም፤ አሽከርካሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው ምዝገባ እንዲያካሂዱ፣ የፈተና ቦታና ሰዓት እንዲያውቁ እንዲሁም ውጤታቸውን በፈጣን መልዕክት እንዲያገኙ ያስችላል።
የሥርዓቱ ትግበራ አሽከርካሪዎችን መዝግቦ፣ አሰልጥኖና ፈትኖ የብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት የሚያስችል ሲሆን፤ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውንና በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን ገልጸዋል።
ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም
