ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱን ለማቆም አሜሪካ ላቀረበችው የሰላም የውል ሃሳብ ኢራን የሰጠችው ምላሽ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል።
የቴህራን የሰላም ሃሳብ፤ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የባህር ሃይል ከበባ እንዲነሳና ለደረሰው ውድመት ካሳ እንዲከፈል የሚጠይቁ ነጥቦችን አካቷል።
ትራምፕ ጦርነቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያበቃል ቢሉም፣ ቤንያሚን ኔታንያሁ ግን ጦርነቱ ሊያበቃ የሚችለው የኢራን የዩራኒየም ማበልጸጊያ ጣቢያዎች ሲፈርሱ ብቻ መሆኑን አስታውቀዋል።
የኢራኑ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን በበኩላቸው ድርድር ማለት “እጅ መስጠት አይደለም” ሲሉ መናገራቸውን ተከትሎ፣ ትራምፕ የኢራንን ሃሳብ “በፍጹም ተቀባይነት የሌለው” በማለት ውድቅ አድርገውታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል ።
ሳራ ዮሀንስ
ግንቦት 03/2018 ዓ.ም
