ሰርጌይ ላቭሮቭ የአውሮፓ ህብረትን የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ንግግር “የማይረባ” ሲሉ አጣጣሉ

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ፤ አዲሷ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ካጃ ካላስ የሩሲያን የጦር ኃይል ለመገደብ የሰነዘሩትን ሃሳብ “የማይረባ” ወይም “ቂልነት” ሲሉ ተችተዋል።

ካጃ ካላስ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፤ ሩሲያ ወደፊት ለጎረቤቶቿ ስጋት እንዳትሆን ወታደራዊ አቅሟ ሊገደብ ይገባል የሚል ፍንጭ ሰጥተው ነበር።

ለዚህ ምላሽ የሰጡት ላቭሮቭ፤ እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ከእውነታው የራቀና የአውሮፓ ህብረት አመራሮች ያለባቸውን የዲፕሎማሲ ግንዛቤ እጥረት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም፥ የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ የሚከተለው የጥላቻ ፖሊሲ በክልሉ ሰላም ለማምጣት እንደማይረዳ ገልጸዋል።

የቀድሞዋ የኢስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ካጃ ካላስ፤በሩሲያ ላይ ባላቸው ጠንካራ አቋም የሚታወቁ ሲሆን፥ በቅርቡ ነበር ጆሴፍ ቦሬልን በመተካት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት።

በሞስኮ እና በብራስልስ መካከል ያለው ግንኙነት በዩክሬን ጦርነት ምክንያት እጅግ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት፤ የሁለቱ ወገኖች የቃላት ጦርነት ይበልጥ እየተካረረ መጥቷል ሲል የዘገበው አል አረቢያ ነው።

ልዑል ወልዴ

ግንቦት 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *