ፓርቲዎች በምርጫ ዙሪያ የሚያቀርቡትን  ቅሬታ እስከ ሰኔ ሁለት ቀን ድረስ ብቻ እንደሚቀበል ቦርዱ  ተነገረ 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በትናትናዉ እለት ማምሻዉን በሰጠዉ እለታዊ መግለጫ እንደተናገረዉ በምርጫዉ ዙሪያ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ህጉ እስከ አስቀመጠዉ ቀነ ገደብ እንደሚቀበል ገልጿል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሀይሉ እስካሁን ባለዉ ጊዜ ቦርዱ የቁጫ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ለቦርዱ ቅሬታዉን ማስገባቱን አረጋግጠዋል።

ግንቦት 24 ቀን በተደረገው ሰባተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ ምርጫዉ ተጭበርብሯል ተብሎ ለቀረበዉ የፓርቲዉ አቤቱታ በቦርዱ የህግ ክፍል የሚታይ መሆኑን ሰብሳቢዋ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

ሰብሳቢዋ እንደገለፁት ፓርቲዎች በምርጫዉ ዙሪያ ለሚያቀርቧቸዉ ቅሬታዎች በህግ እስከተቀመጠዉ ጊዜ ድረስ ቦርዱ የሚቀበል መሆኑን ገልፀዋል።

ቅሬታዎቹ በህግ አግባብ መርምሮ የሚያጣራቸዉ መሆኑን የገለፁት ሰብሳቢዋ ፓርቲዎች የሚያቀርቧቸዉን ቅሬታዎች በማጥራት አስፈላጊውን ዉሳኔ ይሰጣል ብለዋል።

ቦርዱ ባወጣዉ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የቅሬታ ማቅረቢያዉ ቀነገደብ ሰኔ 2 ቀን 2018 አ.ም የሚያበቃ መሆኑን በማሳያዉ ገልጿል።

ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሀይሉ በመግለጫቸው በአሁን ወቅት በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደት መጠናቀቁን እና ዉጤት መለጠፉን ተናግረዋል።

አያይዘዉም ከምርጫ ጣቢያዎች የተሰበሰበው የድምጽ መረጃዎችን ወደ ምርጫ ክልል ሄዶ የመደመር ስራ እየተሰራ ስለመገኘቱ ጠቁመዋል።

በሂደቱ መሠረትም ከምርጫ ክልል የማዳመር ስራ የተጠናቀቀባቸው ወደ ማዕከል የማምጣት ስራ መጀመሩን በመግለጫቸው ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

ቁምነገር አየለ

ግንቦት 27/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *