ኬንያ ውስጥ በደረሰ አሰቃቂ የትምህርት ቤት ቃጠሎ ዘጠኝ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኬንያ በሚገኝ አንድ አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ 16 ተማሪዎችን ለሞት የዳረገውን ቃጠሎ አቅደዋል እና ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ዘጠኝ ሴት ተማሪዎች እስከ 21 ቀናት ድረስ በቁጥጥር ስር እንዲቆዩ ተወሰነ።

መርማሪዎች ምርመራቸውን እንዲያጠናቅቁ እና ክስ መመስረት አለመመስረታቸውን እንዲወስኑ ተጠርጣሪዎቹ በሕፃናት ማቆያ ማዕከል ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዲቆዩ ይደረጋል።

ጉዳዩ የመላው ሀገሪቱን ትኩረት ስቧል።

ቃጠሎዉ ከዋና ከተማዋ ናይሮቢ በ90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጊልጊል፣ ናይቫሻ አቅራቢያ የሚገኘውን እና 2መቶ2 ተማሪዎችን የያዘውን የኡቱሚሺ የሴቶች ትምህርት ቤት የመኝታ ክፍልን አውድሟል።

ዘጠኙ ተጠርጣሪዎች ሁሉም በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ፤ከተማሪዎች የተገኘ የምስክርነት ቃል እና የደህንነት ካሜራ ምስሎችን ከመረመሩ በኋላ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ቃጠሎው የተነሳው ተማሪዎቹ በመኝታ ክፍሉ መውጫ ላይ የሚገኝ ፍራሽ በክብሪት እና በጋዝ በመለኮሳቸው እንደሆነ ተገልጿል።

ለዚህ የቃጠሎ ጥቃት እስካሁን ምንም ዓይነት ምክንያት አልተገለጸም።

ለመለየት በሚያስቸግር ሁኔታ የተቃጠሉ አንዳንድ አስከሬኖችን ማንነት ለማረጋገጥ የሚደረገው የዲኤንኤ ምርመራ ውጤት ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ግንቦት 27/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *