በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተደረሰው ስምምነት በሊባኖስ ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ እንዲቆም ማድረግን እንደሚያካትት ተገለፀ

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረገው ስምምነት የመጀመሪያው አንቀጽ እንደሚያመለክተው አሜሪካ እና አጋሮቿ ሊባኖስን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች ላይ ወታደራዊ ዘመቻዎች በአስቸኳይ እና በቋሚነት እንዲቆሙ ያሳስባሉ፡፡

ይህ ጉዳይ በግጭቱ ውስጥ ዋነኛ የአለመግባባት መንስኤ ሆኖ የቆየ ሲሆን፤ በሊባኖስ የሚንቀሳቀሰው እና በኢራን የሚደገፈው የታጠቀው ቡድን ሄዝቦላህ እንዲሁም እስራኤል የተኩስ አቁም ቃልኪዳኖችን በመጣስ እርስ በእርስ ሲወነጃጀሉ ቆይተዋል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋኢ ቀደም ብለው በቴሌግራም ገጻቸው ላይ እንደገለጹት፤እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርገውን ጥቃት ከቀጠለች ድርጊቱ የመግባቢያ ስምምነቱን እንደመጣስ ይቆጠራል።

እንደ ኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ዘገባ የደህንነት ቃል አቀባዩ የእስራኤል ጦር በሊባኖስ መቆየቱ ጦርነቱን ለማቆም የተደረገውን ስምምነት መጣስ ነው ማለታቸውንም ገልጸዋል።

የእስራኤል ጦር ትናንት በደቡባዊ ሊባኖስ አዳዲስ ጥቃቶችን የፈጸመ ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ በደቡባዊ ሊባኖስ በተከሰተ ክስተት የቆሰለ አንድ ወታደር መሞቱን አስታውቋል።

በትናንትናው ዕለት በፈረንሳይ በተካሄደው የቡድን 7 ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሊባኖስ ሰላም ማስፈን ልንሰራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን ብለው ሆኖም ግን ትልቁ ስምምነት የኢራኑ ስምምነት ነው ብለዋል።

የእስራኤል መንግሥት ስለ አሜሪካ እና ኢራን ስምምነት መፈረም እስካሁን በይፋ የሰጠው ምላሽ የለም።

ሀና ሰይፉ

ሰኔ 11/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *