የኢትዮጵያ ንግድ ስራ ኮርፖሬሽን ያቋቋማቸው አብዛኞቹ መሸጫ መደብሮች ለሽያጭ ፍጆታ የሚቀርብ ሸቀጥ የላቸዉም ተባለ

ኮርፖሬሽኑ የገበያ ማረጋጋት ኃላፊነቱን በተገቢው መንገድ መወጣት አለመቻሉን የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያቤት ሪፖርት አሳይቷል።

ሪፖርቱ እንደሚጠቁመዉ ካለፉት የ2015 እና 2016 በጀት ዓመታት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የኮርፖሬሽኑ የምርት ግዥ በዓይነትና በመጠን የማሳደግ አፈፃፀም ቅናሽ ያሳየ መሆኑ ተጠቁሟል።

ከዚህ ባለፈ ኮርፖሬሽኑ መሰረታዊ ሸቀጦችን በማቅረብ የገበያ ማረጋጋት ሥራን ለመስራት ያቋቋማቸው የመሸጫ መደብሮች ውስጥ የሚገኙ አብዛኛዎቹ መደርደሪያዎች ባዶ ወይም ምንም ዓይነት ለሽያጭ የሚቀርብ የፍጆታ ሸቀጥ የሌላቸው መሆኑን ሪፖርቱ አሳይቷል።

በሌላ በኩል የተለያዩ ሸቀጦች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ሳያበቃ አማራጭ የሽያጭ ዘዴዎችን በመጠቀም እንዲሸጡ ባለማድረጉ ምርቶቹ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ መሆኑን ተረጋግጧል።

ለማሳያም ኮርፖሬሽኑ በመርካቶ፣ በቃሊቲ፣ ሻሸመኔ እና ሐዋሳ የመሸጫ መደብር አጠቃላይ ድምር ዋጋቸው ብር 12 ሚሊዮን 139 ሺህ 6 መቶ 25. የሚያወጡ ሸቀጦች ይገኙበታል ተብሏል

በኮርፖሬሽኑ የግዥ መመሪያ በዋጋ ማቅረቢያ የግዥ ዘዴ ለመግዛት ከተፈቀደው ብር አንድ ሚሊዬን ጣራ በላይ በ2016 ዓ.ም 1መቶ37 ሚሊየን 7መቶ 12 ሺህ 9መቶ 60 ብር የደብተር ግዥ መፈፀሙን ተረጋግጧል።

ሪፖርቱ እንደገለፀዉ ከተገዛው ደብተርም 67 ሚሊየን 79ሺህ 4መቶ30 ብር የሚሆነዉ ኦዲቱ እስከተጠናቀቀበት ጊዜ ድረስ አለመሸጡን ገልፆል።

ቁምነገር አየለ

ሰኔ 12/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *