የዚምባብዌ ሴኔት ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋጓን እስከ 2030 በሥልጣን ላይ ሊያቆዩ የሚችሉ አወዛጋቢ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያዎችን በከፍተኛ ድምፅ አፅድቋል።
ይህም ማሻሻያዎቹ ቀደም ሲል ከታችኛው ምክር ቤት ፈቃድ ካገኙ በኋላ ሙሉ የፓርላማ ድጋፍ እንዲያገኙ አድርጓቸዋል።
የሴኔቱ ፕሬዝዳንት ሜብል ቺኖሞና 75 ሴናተሮች ደግፈው ሲመርጡ አራት ሴናተሮች ደግሞ ተቃውመው መምረጣቸውን ገልጸዋል።
ረቂቅ ሕጉ ሰኔ 18 ቀን በብሔራዊ ምክር ቤቱም ያለፈ ሲሆን፤ በወቅቱ 2መቶ16ቱ ደግፈው 42ቱ ደግሞ ተቃውመው ድምፅ ሰጥተው ነበር።
ረቂቅ ሕጉ በምናንጋጓ ተፈርሞ ሕግ ሆኖ ከመውጣቱ በፊት በቴክኒካዊ ማስተካከያዎች ላይ ለመስማማት ወደ ብሔራዊ ምክር ቤቱ መመለስ እንዳለበት አንድ ባለሥልጣን ተናግረዋል።
በተቺዎች ‹‹ሕገ-መንግሥታዊ መፈንቅለ መንግሥት›› ተብሎ የተገለጸው ይህ ሰፊ ለውጥ፤ የፕሬዝዳንቱን እና የፓርላማውን የሥልጣን ዘመን ከአምስት ዓመት ወደ ሰባት ዓመት የሚያራዝም ድንጋጌን ያካትታል።
ይህም ማለት በሕገ-መንግሥቱ የተገደበው የምናንጋጓ የመጨረሻው ሁለተኛ የሥልጣን ዘመን እስከ 2030 ድረስ ይራዘማል ማለት ነው።
ሌላው ማሻሻያ ደግሞ አገሪቱ ነፃነት ካገኘች ከሰባት ዓመት በኋላ በ1987 የተጀመረውን ቀጥተኛ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በማስቀረት ፓርላማው ፕሬዝዳንቱን የመሾም ሥልጣን እንዲኖረው ያደርጋል።
እስከዳር ግርማ
ሰኔ 18/2018 ዓ.ም
