የሰላምና መረጋጋት እጦት በሀገሪቱ የትምህርት ዘርፍና በትውልድ ግንባታ ላይ እያሳደረ ያለው ጫና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የፓርላማ አባሉ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ አመላከቱ።
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚስተዋሉ የትጥቅ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ዜጎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው እንዳይማሩና እንዳያስተምሩ ትልቅ ዕንቅፋት ፈጥረዋል።
እንደ ዶክተር ደሳለኝ ገለጻ፣ እውነተኛና አካታች የሆነ የፖለቲካ መፍትሔ ሳይመጣ እንዲሁም የታጠቁና ያልታጠቁ ኃይሎችን ያካተተ የምክክር ሂደት ሳይመሰረት ዘላቂ ሰላም ማምጣት አይቻልም።
ይህ ሰላም በሌለበት ሁኔታ ደግሞ የትምህርት ተደራሽነትን ማረጋገጥም ሆነ ጥራቱን የጠበቀ ትውልድ ማፍራት የማይታሰብ መሆኑን አስገንዝበዋል።
መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት የተከተለውን የፖለቲካ ችግሮችን በኃይል የመፍታት መንገድ በአስቸኳይ በመተው፣ ወደ ሰለጠነ የፖለቲካ ድርድር እንዲሻገርና በትጥቅ ግጭቶች ሳቢያ አደጋ ላይ የወደቀውን የትውልዱን መፃኢ ተስፋ እንዲታደግ በጥብቅ አሳስበዋል።
ልዑል ወልዴ
ሰኔ 30/2018 ዓ.ም
