ኢራን ባለፉት ሁለት ቀናት በተሰነዘሩባት የአሜሪካ ጥቃቶች የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገለጸች 

የኢራን ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ የአሜሪካ ጦር ኃይሎች ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በሀገሪቱ አምስት ግዛቶች ላይ ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን፣ በዚህም የ14 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 78 ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል።
 
በሌላ በኩል ኢራን በባህሬን፣ ኩዌት እና ኳታር ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃቶችን መፈጸሟን ገልጻለች፡፡
 
የኢራን ወታደራዊ ኃይል ከአንድ ሰዓት በፊት በባህረ ሰላጤው አካባቢ የሚገኙ “የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን እና ስትራቴጂካዊ ማዕከላትን” ኢላማ ያደረጉ የድሮን ጥቃቶችን ማድረሱን አስታውቋል።
 
ጥቃቶቹ በኩዌት የሚገኘውን የፓትሪዮት ሚሳይል መከላከያ ሥርዓት፣ በኳታር የሚገኘውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሳተላይት አንቴና ጣቢያ እንዲሁም በባህሬን የሚገኙ የአሜሪካ ጦር የነዳጅ ታንከሮችን ኢላማ ያደረጉ ነበሩ።
 
የኢራን ወታደራዊ ኃይል በጥቃቶቹ ላይ “በብዛትና በአይነት የተለያዩ በርካታ ድሮኖችን” ጥቅም ላይ ማዋሉን ገልጿል እንደ ፎክስ ኒውስ ዘገባ።
 
ሐምሌ 02/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *