ባለፉት 12 ወራት ከ1ሺ 6መቶ ኪሎ ሜትር በላይ የግንባታና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት 1 ሺህ 6መቶ 66 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍኑ ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች ማከናወኑን ገልጿል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ 1ሺ3መቶ3 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የግንባታና የጥገና ስራዎች ለማከናወን አቅዶ፤በዕቅድ ከተያዙ ሥራዎች በተጨማሪ በርካታ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎችን መስራቱን አስታዉቋል፡፡

ከዚህም ውስጥ ከ3መቶ46 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍነው ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታ ስራ ሲሆን፤በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የተገነቡ መንገዶችን ጨምሮ 69 ኪሎ ሜትር የአስፋልት፣ 61 ኪሎ ሜትር የጠጠር እና 108 ኪሎ ሜትር የኮብል ንጣፍ መንገድ ስራ ይገኝበታል ተብሏል፡፡

ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *