የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በዋይት ሀውስ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የሚገናኙ ሲሆን፥ በዋናነትም በኢራን ላይ የተከፈተው ጦርነት በአጀንዳነቱ ቀዳሚ ቦታ ይይዛል።
ይህ ጉብኝት ሁለቱ ሀገራት በየካቲት ወር በቴህራን ላይ ጥቃት በመሰንዘር ጦርነቱን ከጀመሩ ወዲህ ኔታንያሁ ከትራምፕ ጋር የሚያደርጉት የመጀመሪያው ውይይት ነው።
በተጨማሪም ጉብኝቱ በዌስት ባንክ የእስራኤል ወረራ እና እስራት በበረታበት እንዲሁም ከሶስት ወራት በኋላ በእስራኤል ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት ላይ መሆኑ ትኩረት ስቧል።
የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ኔታንያሁ ለምርጫው የትራምፕን ድጋፍ ለማግኘት እየጣሩ ነው።
ኔታንያሁ ወደ አሜሪካ የመጡት በሐምሌ 11 ቀን በሞቱት የሪፐብሊካን ሴናተር ሊንድሴ ግራሃም የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመገኘት ሲሆን፥ የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት ከመጀመሩ በፊት ከትራምፕ ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ይዘዋል።
በውይይቱም ላይ ከኢራን ጦርነት በተጨማሪ በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል ስላለው ግጭት እንዲሁም የአብርሃም ስምምነትን ስለማስፋፋት እንደሚመክሩ ተገልጿል።
ሆኖም የሁለቱ መሪዎች የውይይት ውጤት ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ተብሎ አይጠበቅም ተብሏል።
ሳራ ዮሐንስ
ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም
