የኢትዮጵያ አየር መንገድ 9 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ማግኘቱን አስታወቀ

አየር መንገዱ የፈረንጆቹ 2025-2026 የስራ ክንውን ሪፖርቱን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ፤ በአጠቃላይ ይህ አመት ለአየር መንገዱ ጥሩ የሚባል ዓመት እንደሆነ አንስተዋል።

ነገር ግን ባለፉት ወራት በገልፍ እና በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር እንዲሁም በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ያጋጠመው ቀውስ ለነዳጅ ማጓጓዝ ሂደቱ ፈተና ሆኖ ማለፉን ጠቅሰዋል።

በአመቱ 4 አዳዲስ በረራዎችን በመጨመር በአጠቃላይ 1መቶ50 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ላይ መደረሱን አንስተዋል።

22 የነበረውን የሀገር ውስጥ መዳረሻም ወደ 25 ከፍ ማድረግ እንደተቻለ ተገልጿል።

በዚሁ አመት 9 አዳዲስ አውሮፕላሮች በኪራይ እና በግዢ አየር መንገዱን መቀላቀላቸውም ተነግሯል።

አየር መንገዱ 20.7 ሚሊየን መንገደኞች ማጓጓዙንም አስታውቋል።

በአጠቃላይ አየር መንገዱ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች 9 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ያስታወቀ ሲሆን፤ይህም አሃዝ ከባለፈው ዓመት አንፃር የ20 በመቶ እድገትን እንዳሳየ ተገልጿል።

አየር መንገዱ በቀጣይ አመት ዕቅዱ የገቢውን መጠን ወደ 10 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ እንደሚሰራ ነው የገለፀው።

የዉልሰዉ ገዝሙ

ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *