በቤንች ሸኮ ዞን የአማን ሻሸቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ 6 ነጥብ 4 ኪሎ ግራም የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላግለዋል።
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ቹቹ አረጋ እንደገለጹት፤ እናቲቱ በሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች በተደረገላቸው የቅርብ ክትትል ህጻኗን በቀዶ ህክምና በሰላም መገላገል ችለዋል።
ወ/ሮ ሳይሉሽ ከዚህ ቀደም ከ6 ዓመት በፊት ሁለተኛ ልጃቸውን በወለዱበት ወቅትም አሁንም በተመሳሳይ በቀዶ ጥገና ህክምና 5 ኪሎ ግራም የሚመዝን ህጻን መገላገላቸውን አያይዘው ገልጸዋል።
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
