በ2019 ዓመተ ምህረት የትምህርት ዘመን በግል ትምህርት ቤቶች በሚካሄደው የተማሪዎች ምዝገባ፣ የክፍያ ጭማሪና የግብዓት ጥያቄ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተካሄደ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ::
ባለፉት ዓመታት የግል ትምህርት ቤቶች በወርሃዊ ክፍያ፣ በምዝገባ፣ በዩኒፎርም እንዲሁም በዓይነት በሚጠይቋቸው እንደ ሳሙና እና ሶፍት ባሉ ቁሳቁሶች ምክንያት በወላጆች ዘንድ ሰፊ ቅሬታ ሲነሳ መቆየቱ ይታወሳል
ሐምሌ 24/ 2018 ዓ.ም
