የፍትሕ ሚኒስቴሩ ጊዜያዊ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ቶድ ብላንች፣ አነጋጋሪው የ1.8 ቢሊየን ዶላር የመንግሥት ተቋማት መጠቀሚያነት መከላከያ ፈንድ መሰረዙን ያሳወቁ ሲሆን፤መቀመጫውን በዋሽንግተን ያደረገው የፍትሕ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ ፈንዱ በመጀመሪያ የተቋቋመው በፌዴራል መሥሪያ ቤቶች አላግባብ ኢላማ ተደርገናል ለሚሉ ወገኖች ካሣ ለመክፈል ታስቦ ነው።
ሆኖም የፈንዱ መስፈርት እጅግ ሰፊ በመሆኑ በ2021 በአሜሪካ ካፒቶል ሕንፃ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችንም የካሣ ክፍያው ተጠቃሚ ሊያደርግ ይችላል በሚል ከሕግ አውጪዎች ዘንድ ከፍተኛ ትችት ሲሰነዘርበት ቆይቷል።
ይህ አነጋጋሪ ፈንድ የተቋቋመው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሀገሪቱ የገቢዎች መሥሪያ ቤት ጋር የነበራቸውን የሕግ ክስ በስምምነት በጨረሱበት ወቅት ሲሆን፤ ውሉ የትራምፕን ቤተሰብ ከወደፊት የታክስ ምርመራዎች የሚከላከል ድንጋጌንም ያካተተ ነበር።
ቶድ ብላንች በኤክስ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ እኔና ቡድኔ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ከኮሚቴ አባላት እና ከሴናተሮች ጋር በመገናኘት ማንኛውንም ስጋቶች እና ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ምላሽ ሰጥተናል ፡፡
በበጎ ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ውጤታማ ውይይት አድርገናል በዚህም መሠረት በግንቦት ወር ከተደረገው የIRS ስምምነት ጋር በተያያዘ ይህንን አዲስ ትዕዛዝ እና ማሻሻያ አውጥተናል ብለዋል፡፡
አክለውም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው ከሁሉም የኮንግረስ አባላት ጋር የሚደረግን ውጤታማ እና ገንቢ ግንኙነት ሁልጊዜም እንደሚያከብር ገልጸዋል።
ሀና ሰይፉ
ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም
