ኢትዮጵያ በ2030 የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን ወደ 54 በመቶ ለማድረስ ግብ ማስቀመጧ ተገለፀ

በጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ ጤና የቤተሰብ ዕቅድና የአፍላ ወጣቶች ፕሮግራም ሀላፊ  ዶ/ር አለማየሁ እንዳሉት፥የቅርብ ጊዜው የጤናና ስነ-ህዝብ ጥናት ውጤት እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ የዘመናዊ ቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚነት 35 በመቶ ላይ ይገኛል።

ይህንን ቁጥር በአውሮፓውያኑ 2030 ወደ 54 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት የእናቶች ሞት በ1መቶ ሺህ ወሊድ 1መቶ41 መሆኑንና የለጋ ዕድሜ እርግዝና ደግሞ 10 በመቶ መድረሱ ተመላክቷል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የለጋ ዕድሜ እርግዝናን ወደ 3 በመቶ ዝቅ ለማድረግና የእናቶችን ሞት በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ የወንዶችን ተሳትፎ ማሳደግ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ገልጿል።

በተለይም በገጠር አካባቢዎች የሚስተዋሉ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ተጽዕኖዎችን በመቀነስ ማህበረሰቡ የጤና ተቋማትን እንዲጠቀም የማድረግ ስራ በትኩረት እንደሚሰራም ተገልጿል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *