የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ13ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጤና እንክብካቤ ፌዴሬሽን ጉባኤ እና ዓለም አቀፍ የጤና ኤግዚቢሽን ስፖንሰር መሆኑን ገለፀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ የጤና ፌዴሬሽን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀውን የ13ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጤና እንክብካቤ ፌዴሬሽን ጉባኤ እና ዓለም አቀፍ የጤና ኤግዚቢሽን 2026 ዋና ስፖንሰር በመሆን በይፋ ተሰይሟል።

ባንኩ በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፥ድጋፉን ያደረገው ያለጤናማ ህብረተሰብ ዘላቂ ኢኮኖሚ መገንባት እንደማይቻል በማመኑ እንደሆነ ገልጿል።

በዚህ ምክንያት በጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ከነሐሴ 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄደውን 13ኛውን የምስራቅ አፍሪካ የጤና እንክብካቤ ፌዴሬሽን ጉባኤ እና ኤግዚቢሽን ዋና ስፖንሰር መሆኑን አስታውቋል።

በዚህ አህጉራዊ መድረክ ከ20 በላይ ሀገራት የተውጣጡ 2 ሺህ ያህል መሪዎች፣ የጤና ባለሙያዎችና አምራች ድርጅቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጉባኤው በሕክምና ምርቶች ላይ ከውጭ የሚደረግን ጥገኝነት ለመቀነስ ያለመ ሲሆን፥ባንኩም የሀገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾችን በካፒታል፣ በውጭ ምንዛሬ እና በረጅም ጊዜ ብድር ለማጠናከር እንዲሁም በአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣና ማዕቀፍ ድንበር ተሻጋሪ የጤና ኢንቨስትመንቶችን እንደሚደግፍ አስታውቋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *