ካናዳ በአሜሪካ ምርቶች ላይ አዲስ ቀረጥ ጣለች

ካናዳ ከአሜሪካ ጋር ያላት የንግድ ውዝግብ እየተባባሰ ባለበት ሁኔታ በአሜሪካ ምርቶች ላይ አዲስ ቀረጥ መጣል ጀምራለች።

ከማክሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው እና በአሜሪካ ምርቶች ላይ የተጣለው ቀረጥ ወደ 28 ቢሊዮን የካናዳ ዶላር፣ ወይም ወደ 20 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ ቢቢሲ አስነብቧል።

በቀረጡ ከሚካተቱት ምርቶች መካከል ብረት፣ የቤት ዕቃዎች፣ ልብሶች፣ ኤሌክትሮኒክስና የተለያዩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች ይገኙበታል።

ይህ እርምጃ የመጣው በቅርቡ አሜሪካ በካናዳ ምርቶች ላይ እስከ 50 በመቶ የሚደርስ ቀረጥ መጣሏ ተከትሎ ነው።

አሜሪካ በካናዳ መኪናዎችና የጭነት መኪናዎች ላይ 25 በመቶ ቀረጥ እንዲሁም በብረትና አልሙኒየም ላይ ተጨማሪ ቀረጥ አስቀምጣለች።

የንግድ ግጭቱ በአሜሪካና ካናዳ ንግዶች ላይ ብቻ ሳይሆን በሸማቾችም ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ተገልጿል።

ሁለቱ አገራት የንግድ ግጭቱን በድርድር ለመፍታት ፍላጎት እንዳላቸው ቢገልጹም፣ በነሐሴ መጨረሻ ያቋረጡትን የንግድ ድርድር እስካሁን እንደገና አልጀመሩም።

ሰላማዊት ዲታ

ጳጉሜ 3/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *