በአዲስ አበባ ከተማ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ተመዝግበው በመጀመሪያው ቀን በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች አካባቢውን ሳቢ በማድረግ፣ አስፈላጊ ግብአቶችን በማሟላትና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ቢሮው መምህራንና ርዕሳነ መምህራን ተማሪዎችን በፍቅርና በትምህርት ኮትኩቶ ለማሳደግ በከፍተኛ ፍላጎት ወደ ሥራቸው መመለሳቸውንም ገልጻል፡፡
የትምህርት ጥራትን፣ ሰላማዊነትንና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ የከተማው ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
መስከረም 6/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ለትምህርት ገበታ ተመዝግበዋል
