አሜሪካ የፍልስጤሙ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ኒውዮርክ በሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዳይሳተፉ የመግቢያ ቪዛ ከለከለች።
አሜሪካ ለአባስ ቪዛ ስትከለክል የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፍልስጤም ባለስልጣናት ላይ የተጣለውን የቪዛ ማዕቀብ እንደሚያራዝም ያስታወቀ ሲሆን፣ እርምጃው የተወሰደው ፍልስጤም የእስራኤል-ፍልስጤምን ግጭት ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች በመውሰድ “ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ ባደረገችው ጥረት” ምክንያት መሆኑን ገልጿል።
በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ስር አሜሪካ ባለፈው ዓመትም ለአባስ ተመሳሳይ ቪዛ በመከልከል በጉባኤው ላይ በአካል ተገኝተው ንግግር እንዳያደርጉ አግዳቸው ነበር።
በአሁኑ ወቅት 193 አባላት ያሉት የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ፕሬዝዳንት አባስ በስብሰባው ላይ በቪዲዮ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል።
መስከረም 8/2019 ዓ.ም
You need to add a widget, row, or prebuilt layout before you’ll see anything here. 🙂
