አዲስ አበባ መካሄድ የጀመረው 9ኛው የአፍሪካ የጉበት በሽታዎች ኮንፈረንስ (COLDA 2026) የጉበት በሽታን ለመከላከልና እ.ኤ.አ በ2030 የተጣለውን አህጉራዊ ግብ ለማሳካት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገለጸ።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በጉባኤው ላይ እንደተናገሩት፣ መንግስት በሽታውን ለመከላከል በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፦
መድኃኒቶች በመንግስት በጀት ተገዝተው በነፃ የሚታደሉ ሲሆን፣ አዲስ ለተወለዱ ህጻናት በሚሰጥ የሄፓታይቲስ ቢ ክትባት ከ90% በላይ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
በሽታው ወደ ካንሰርነት እንዳይቀየር አስቀድሞ ለመመርመርና ካንሰርን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለመለየት እየተሰራ ነው ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው ።
አክለውም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የመጀመሪያውን የጉበት ንቅለ-ተከላ ህክምና ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው።
የኢትዮጵያ ጋስትሮአንትሮሎጂ ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጂግሳ ዳበሳ በበኩላቸው፣ ጉባኤው በምርምር፣ በባለሙያዎች ስልጠና እና ቅድመ-ምርመራን እስከ ታችኛው የጤና መዋቅር ለማውረድ በሚደረጉ ስራዎች ላይ አህጉራዊ ቅንጅትን እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
መስከረም 8/2019 ዓ.ም
የጉበት በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለው አህጉራዊና ሀገራዊ ጥረት ተጠናክሩ መቀጠሉ ተገለጸ
