የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት እና ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ትስስር መድረክ ሊካሄድ ነው

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ዓመታዊ ዋና መድረክ የሆነው የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት  ከመስከረም 19 እስከ 21 ቀን በአዲስ አበባ፣  ስካይ ላይት ሆቴል በደመቀ ሁኔታ እንደሚካሄድ ተገልጿል ።

​በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ ሁነት ላይ ከመላው ዓለም ከ20 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ100 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ተሳታፊዎች ፣ ባለሀብቶች እና የዘርፉ ባለሙያዎች ይገኙበታል ተብሏል ።

ዝግጅቱ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን፣ የቢዝነስ  እና የኢንቨስትመንት ስብሰባዎችን፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ዲጂታል ቱሪዝምን ጨምሮ ወቅታዊ የፖሊሲ ውይይቶችን ያካተተ መሆኑ ተነግሯል ።

​በተጨማሪም የኦሮሚያን ሰፊ የባህል ሀብት የሚያስተዋውቁ የፋሽን፣ የሙዚቃ፣ የስነ-ጥበብ እና የእደ-ጥበብ ትርኢቶች፣ በዘርፉ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የሚሰጠው የኦሮሚያ ቱሪዝም ሽልማት፣ እንዲሁም “የሚስ ቱሪዝም ኦሮሚያ 2026” ውድድርም  የዝግጅቱ አካል እንደሆኑ ተጠቅሷል ።

​ይህ መድረክ የኦሮሚያን የቱሪዝም እምቅ አቅም ለዓለም ከማስተዋወቅ ባለፈ አዳዲስ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትስስሮችን የሚፈጥር በመሆኑ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ዝግጅቱን በቅርበት እንዲዘግቡት ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

ሀመረ ፍሬው

መስከረም 12/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *