የጨፌ ኦሮሚያ አዲሱን የክልሉን አደረጃጀት ይፋ አደረገ።

ጨፌው ዛሬ እያካሄደ ባለው  7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው ቀደም ሲል  በ21 ዞኖች ተደራጅቶ የነበረውን የዞኖች አደረጃጀት ወደ ስድስት ዝቅ አድርጓል።

አደረጃጀቱ «የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ታሪካዊ ውሳኔ» ያሉት ዛሬ ተሹመው ስራ ከጀመሩት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጉዮ ዋሪዮ ናቸው።

በክልሉ የአካባቢ መጠሪያ የነበራቸው ሰብሰብ ተደረገው በአቅጣጫቸው መሰረት የኦሮሚያን ስም ከፊት እያስቀደሙ ይጠራሉ ።

በዚሁ መሰረት ስድስቱ የክሉ ዞኖች ፤ የኦሮሚያ ምስራቅ ዞን፣ የኦሮሚያ ማዕከላዊ ዞን፣  የኦሮሚያ ምዕራብ ዞን፣ ኦሮሚያ ደቡብ ዞን፣ የኦሮሚያ ደቡብ ምዕራብ ዞን እና የኦሮሚያ ደቡብ ምስራቅ ዞን መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

መስከረም 18/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *