የካሊፎርኒያ ጓደኛሞች የሌጎ ካርታ ሪከርድን ሰበሩ

​ሁለት የካሊፎርኒያ ጓደኛሞች 11,695 ቁርጥራጮች ያሉት ግዙፉን የሌጎ  የዓለም ካርታ በ4 ሰዓት ከ59 ደቂቃ እና ከ51 ሰኮንዶች ውስጥ ብቻ በመገጣጠም አዲስ የጊነስ የዓለም ሪከርድ አስመዝግበዋል።

​አቲና ሊዮንግ እና ሴቪ ስዊፍት የተባሉት ሁለቱ ወዳጆች፣ ይህንን ታላቅ ውድድር ያከናወኑት  በሃይዋርድ በሚገኘው “ብሪክ ባይ ብሪክ ቶይስ” የተሰኘ መደብር ውስጥ ነው።

ለዚህ ፈተና ለአንድ ሙሉ ወር ያህል ተግተው የተለማመዱት ሁለቱ ወጣቶች፣ በልጅነታቸው ከሌጎ ጋር የነበራቸው ጥልቅ ትዝታና የፈጠራ ፍቅር ዛሬ ላይ ለአንድ ዓላማ አብረው እንዲቆሙ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።

​ጊነስ የዓለም ሪከርድ ድርጅት ያስቀመጠው የ5 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ግብ በሰዓቱ እንዲሳካ ካደረጉዋቸው ዋና ዋና ምስጢሮች መካከል፣ ቀለሞችን በቅደም ተከተል አንድ በአንድ በመያዝ መገጣጠም እንደሚገኙበት ገልጸዋል።

ይህ ስልት ክፍት ቦታዎችን በቀላሉ ለመሙላትና ከፍተኛ ጊዜን ለመቆጠብ እንደረዳቸውም አስረድተዋል።

​በውጤቱ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹት ሁለቱ ጓደኛሞች፣ በቀጣይም ከዚህም የበለጠ ትልቅና ፈታኝ የሆኑ የሌጎ ስብስቦችን በመሥራት አዳዲስ ዓለም አቀፍ ሪከርዶችን ለመስበር ዕቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል ሲል ዩናይትድ ፕረስ ኢንተርናሽናል ዘግቧል።

ሐመረ ፍሬው

መስከረም 20/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *