መንግስት በአመት ለቢሮ ኪራይ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያወጣ ተነገረ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር የበጀት ጉዳዮች አማካሪ አቶ ተፈሪ ደመቀ እንዳስታወቁት፤ አገሪቱ ከምትይዘዉ አጠቃላይ አመታዊ በጀት ዉስጥ 1.2 ቢሊዮን ብሩ ለቢሮ ኪራይ ይዉላል፡፡

መንግስት ለቢሮ ኪራይ በአመት የሚያወጣዉን ወጪ ከቅርብ አመታት ወዲህ እየቀነሰ ቢሆንም አሁንም ድረስ ግን ከፍተኛ በጀት ለኪራይ እንደሚወጣ ተነግሯል፡፡

ይህም የሆነበት ምክንያት የመንግስት ቢሮዎች በተፈለገዉ መልኩ ባለመደራጀታቸዉ እና ለመንግስት መስሪያ ቤቶች ተብለዉ የሚገነቡ ህንፃዎች በመጓተታቸዉ ነዉ ተብሏል፡፡

በመሆኑም በቀጣይ የኮንስራክሽኑን ዘርፍ በመደገፍ የተጀመሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ግንባታን በማፋጣን ለኪራይ የሚወጣዉን 1.2 ቢሊዮን ብር ማዳን እንደሚገባ አቶ ተፈሪ አንስተዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት 10 የፌደራል ተቋማት ቢሮ ተገንብቶላቸው ወደ ራሳቸው ቢሮ የገቡ ሲሆን ሌሎችም እየተገነባላቸው ይገኛል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2014 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 561 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን በቀጣይ መንግስት ለቢሮ ኪራይ የሚያወጣዉን ወጪ መቀነስ እንደሚገባዉም ተነግሯል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *