ዶክተር ዮሃንስ አያሌው የአማራ ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሸሙ

በቅርቡ  ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንትነት ስራቸው የለቀቁት  ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ሹመቱ ከዛሬ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተሠጠ መሆኑን ባንኩ አሳውቋል።

ፕሬዝዳንቱ ስራቸውን የለቀቁት “በፈቃዳቸውና በግል ምክንያት” መሆኑን መናገራቸው የሚታወስ ነው ።

በስራ ዘመናቸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ  ከነበረበት ውስብስብ ችግርና ክስረት ወደ ተሻለ አቋም እንዲመለስ ማስቻላቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች ይመሰክሩላቸዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *