English Premier league Matchweek 19

ሊቭርፑል  ኖቲንግሀም  እና ማንችስትር ሲት ድል ቀንቷቸዋል ቶተንሀም በበኩሉ ነጥብ ጥሏል ፡፡

በአስራ ዘጠነኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብሮች

ሊቨርፑል ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር ያደርጉትን ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሽንፈዋል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ ሳላህ ፣ አርኖልድ ፣ ኮዲ ጋክፖ ፣ ሉዊስ ዲያዝ እና ዲያጎ ጆታ ከመረብ አሳርፈዋል።

ግብፃዊው የሊቨርፑል ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በውድድር ዘመኑ አስራ ሰባተኛ የሊግ ግቡን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል።

ማንችስተር ሲቲ ከሌስተር ሲቲ ጋር ያደረገው ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

ማንችስተር ሲቲን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ እና ሳቪንሆ አስቆጥረዋል።

ብራዚላዊው ተጨዋች ሳቪንሆ የማንችስተር ሲቲ የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ አስራ አራተኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

የአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ማንችስተር ሲቲ ከአራት ተከታታይ የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል ተመልሷል።

በፕርሚየር ሊጉ ጥሩ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ኖቲንግሀም ፎረስት ከኤቨርተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

ኖቲንግሀም ፎረስት ከ 29 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አምስት ተከታታይ የፕርሚየር ሊግ ድሉን ማሳካት ችሏል።

ኖቲንግሀም ፎረስት ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰላሳ ሰባት በማድረስ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

ቶተንሀም  ከዎልቭስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

እንዲሁም በሌሎች ጨዋታዎች

  • ክሪስታል ፓላስ ሳውዝሀምፕተንን 2ለ1 ሲያሸንፍ
  • ፉልሀም ከበርንማውዝ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ዛሬም ሊግ  ሲቅጥል

ምሽት   04፡45  ቼልሲ ከ  ኢፕ ስዊች ታውን

ምሽት   05፡00
ማንችስተር ዩናይትድ  ከ ኒውካስል 

ኢሮብ ምሽት 2:30

  ብሬንትፎርድ    ከ  አርስናል

ጋዲሳ መገርሳ

ታኀሣሥ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *