ኢትዩጲያዊያንን ጨምሩ በአሳሳች የሥራ ዕድል ተታለው በምያንማር በአስከፊ ሆኔታ ውስጥ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች ነጻ መውጣታቸው ተነገረ

ከምያንማር የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ ማዕከላት ነፃ ወጡ ከተባሉት 250 በላይ ዜጎች ውስጥ ኢትዩጲያዊን ይገኙበታል ከሚለው ውጪ ቁጥራቸው አልተገለጸም፡፡

እነዚህ ዜጎች በደላሎች እየተጭበረበሩ የአውሮፕላን ቲኬት ተቆርጦላቸው፣ ሕጋዊ ተጓዥ ሆነው የሄዱ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

ሰራተኞቹ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከአፍሪካ ወይም ከእስያ ሀገራት የመጡ መሆናቸውን ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል፡፡

ዘገባው ጨምሮ እንዳው አሁን እኚህ ታጋቾች የታይላንድ ጦር እንደተቀበላቸው ተነግሯል፡፡

ባለፈው ሳምንት የታይላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔቶንግታርን ሺናዋትራ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር ተገናኝተው በታይ-የምያንማር ድንበር ላይ የተንሰራፋውን የማጭበርበሪያ ማዕከላትን ለመዝጋት ቃል ገብተዋል ነበር ።

የታይላንድ መንግስት ከምያንማር የድንበር አካባቢ የኃይል እና የነዳጅ አቅርቦትን ማቋጡን ገልጻል ፡፡ የባንክ እና የቪዛ ህጎችን በማጠናከርም ወንጀሉን ለመከላከል እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

በተጨማሪም አጭበርባሪ ኦፕሬተሮች የታይላንድን ሰራተኞችን እና ገንዘብን ለማዘዋወር እንደ መሸጋገሪያ ሀገር እንዳይጠቀሙ ለማድረግ የተጠናከረ ስራ እየሰራ እንደሆነ አሳውቋል፡፡

በታይላንድ የሚገኙ አንዳንድ ተቃዋሚ የፓርላማ አባላት ላለፉት ሁለት አመታት እንዲህ አይነት እርምጃ እንዲወሰድ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በአሳሳች የሥራ ዕድል ተታለው ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ፊሊፒንስ፣ ማሌዥያ፣ ፓኪስታን፣ ቻይና፣ ኢንዶኔዥያ፣ ታይዋን፣ ኔፓል፣ ኡጋንዳ፣ ላኦስ፣ ብሩንዲ፣ ብራዚል፣ ባንግላዲሽ፣ ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ፣ ሰርላንካ፣ ህንድ፣ ጋና እና ካምቦዲያ የሄዱ 221 ወንዶች እና 39 ሴቶች ከተለቀቁት ውስጥ ይገኙበታል ሲል ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል።

የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *