በ9 ወራቱ ከ1ሺ 5መቶ በላይ የንግድ መስጫ መደብ ወደ 5መቶ50 ዝቅ ማድረጉንም አስታዉቋል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ፤ከ1ሺ 3መቶ በላይ የንግድ ፍቃድ መስጫ መደቦችን ወደ አስር ዝቅ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
የቅድመ ብቃት ማረጋገጥ ስራ የሚሰሩ 32 ተቋማትን በመቀነስ በአራት ተቋማት ብቻ አገልግሎቱ እንዲሰጥ ማድረግ መቻሉን ሚኒስትሩ አስታዉቀዋል።
ቀናትና ሳምንታትን ይወስድ የነበረውን አዲስ ንግድ ፍቃድና እድሳት በደቂቃዎች እንዲሰጡ ማድረግ መቻሉንም ተናግረዋል።
በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተደራሽ ያደረገ የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፍቃድ ተግባራዊ አድርገናል ብለዋል፡፡
የዚህ ዓመት አፈጻጸም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ6መቶሺህ ብልጫ እንዳለውም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም
