የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያ እና ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምክንያት የነበራቸውን “ግጭት” በማስቆም “ሰላም” ማምጣታቸውን ተናገሩ።
ትራምፕ ይህንን ያሉት በሥልጣን ዘመናቸው ጣልቃ በመግባት ያስቆሟቸውን ግጭቶች በመዘርዘር እሁድ ሰኔ 8/2017 ዓ.ም. ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸውን ባሰፈሩት ጽሁፍ ነው።
ትራምፕ፤ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተቀሰቀሰውን የእስራኤል እና የኢራን ግጭትን ትኩረት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሁለቱ ሀገራት ስምምነት ላይ መድረስ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ሕንድ እና ፓኪስታን በቅርቡ ገብተውበት የነበረውን ግጭት “ከአሜሪካ ጋር የሚደረግን ንግድ” በመጠቀም፤ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ወደ “ምክንያታዊነት፣ ቅንጅት እና ቀልባቸው” እንዲመጡ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ “ሁለቱ ምርጥ መሪዎች በፍጥነት መወሰን እና መቆም ችለዋል” ሲሉ የነበራቸውን ሚና ገልጸዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸውም በሰርቢያ እና ኮሶቮ መካከል “ለአስር ዓመታት” የቆየውን እና “ጦርነት ሆኖ ሊፈነዳ ጫፍ ደርሶ የነበረውን ግጭት” ማስቆማቸውን ጠቅሰዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
