ክረምቱ ሲጠናቀቅ የህዳሴ ግድብ ይመረቃል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን የተናገሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡
ከመመረቁ በፊት ለመረበሽ የሚያስቡ ሰዎች አሉ እኛ ግን እናስመርቃለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ላይ ግድቡ እንዳይመረቅ የሚያደርግ ነገር የለም ለሱዳንም ይሆን ለግብፅ በረከት እንጂ ጉዳት አያመጣባቸውም ብለዋል ።
እንዲሁም ለግብፅ ፣ለሱዳን እንዲሁም ለተፋሰሱ ሀገራት መንግስታት በሙሉ መስከረም ወር ላይ ህዳሴ ግድቡ ሲመረቅ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ የሚል ግብዣቸውንም አቅርበዋል ።
ሐመረ ፍሬው
ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
