የደቡብ አፍሪካ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ ዩናይትድ ስቴትስ በጣለችው የ30 በመቶ ታሪፍ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ስራዎች አደጋ ላይ ናቸዉ፡፡
ታሪፉ የአውቶሞቲቭ ፣ግብርና እንዲሁም ሌሎች የንግድ ዘርፎችን እንደሚጎዳ ገልጿል።
በአሁኑ ጊዜም በዚህ ምክንያት ወደ 30ሺህ የሚጠጉ ስራዎች ሊጎዱ ይችላሉ ብሏል፡፡
ባለፈው ሐሙስ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ነሀሴ 1 ቀን ከመድረሱ ከሰዓታት በፊት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አገሮች ላይ አዲስ ታሪፍ መጣላቸው ይታወቃል።
አንዳንድ ሀገራት የተሻሻሉ የታሪፍ መጠን ቢደረግባቸውም፤ ደቡብ አፍሪካ ቀደም ሲል በታቀደው 30 በመቶ ታሪፍ ምክንያት ከፍተኛ ታሪፍ ከተጣለባቸዉ አምስት ሀገራት ውስጥ አንዷ ሆናለች።
ዩናይትድ ስቴትስ ለደቡብ አፍሪካ ከአውሮፓ ህብረት 17 በመቶ እና ከቻይና 11 በመቶ በመቀጠል ሶስተኛዋ ትልቅ የንግድ አጋር ናት፡፡
አገሪቱ ቀድሞውኑ በከፍተኛ የስራ አጥነት እየታገለች ሲሆን፤ መንግስት በአዲሱ ቀረጥ ምክንያት ለተጎዱ ላኪዎች ድጋፍ ለመስጠት እንደታቀደ ገልጿል፡፡
ታሪፎቹ ከነሐሴ 8 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናሉ መባሉን የዘገበዉ አፍሪካ ኒዉስ ነዉ፡፡
ኤርሚያስ ገረመዉ
ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም
