ተማሪዎች የዩንቨርሲቲዎችን ህግና ደንብ አክብረው በየግቢያቸው እንዲቆዩ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አሳስበዋል።

ከዚህ በተጨማሪም መረጃን የማይሰጡ ዩንቨርሲቲዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስበዋል ።

በጎንደር ዩንቨርሲቲ እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክር ቤት ጉባዔ ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩንቨርሲቲዎች ስለተማሪዎችና ስለመምህራን አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጡ አሳስበዋል።

ተቋማቱ በአጭር ጊዜ የተማሪዎችንና አጠቃላይ የሰው ኃይላቸውን ቁጥራዊ መረጃ ለሚኒስቴሩ እንዲልኩ አስጠንቅቀዋል።

በሚቀጥሉት አራት ወራት ውስጥ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያገልግል የመረጃ ማዕከል ሥራ እንደሚጀምር አስታውቀዋል ።

ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው ይህ የመረጃ ማዕከል 3 ቢሊየን ብር ተመድቧል ብለዋል።

የመምህራን ዝውውርን በተመለከት ዩንቨርስቲዎች መምህራንን በቀላሉ መልቀቅ እንደሌለባቸው አሳስበዋል።
የመውጫ ፈተናን ማሰረቅ ከዩንቨርስቲዎች የማይጠበቅ ትልቅ ጥፋት እንደሆነ አስገንዝበዋል ።

የሬሜዲያል ፈተናን በተመለከተም ሥርቆት እንደሚስተዋል አንስተው ይህም ለዩንቨርሲቲዎን መልሶ የሚጎዳ ነው ብለዋል።

ዩንቨርስቲዎች የሚጠበቅባቸውን ታማኝነት እንዲስጠብቁም ተነስቷል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክርቤት ጉባኤ በጎንደር ዩንቨርሲቲ አስተናጋጅነት መካሄዱን ቀጥሏል።

ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *