ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ድርጅቱ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል።
ጠንካራ እና ሰላማዊ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስተዋጽኦ አላቸው ያሉት የድርጅቱ ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ሁሴን፤ አገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
በዚህ የሰላም ኮንፈረንስ ድርጅቶቹ ለሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ወደ ሰላም እንዲመጡ፣ የትጥቅ ግጭቶች እንዲቆሙ እና ሁሉንም ያሳተፈ ሀገራዊ ምክክር እንዲቀጥል ጥሪ ያቀርባሉ ብለዋል።
ኮንፈረንሱ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሰላም ግንባታ ዙሪያ አጀንዳዎችን ለማዘጋጀት እና የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ገልፀዋል።
ይህ የሰላም ኮንፈረንስ በአዲስአበባ በያዝነው ወር መጨረሻ ነሀሴ 29 የሚደረግ መሆኑንም ተናግረዋል።
በመዲናዋ በሚካሄደው በዚህ መድረክ 3መቶ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ይህን የሰላም ኮንፈረንስ ወደ ተለያዩ ክልሎች ለማስፋት ዕቅድ መያዙ የተገለፀ ሲሆን፤ ትግራይ ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል እንዲሁም ሶማሌ ክልሎች ተከታታይ መድረኮች የሚደረግባቸው መሆናቸው ተገልጿል።
እስከዳር ግርማ
ነሐሴ 16 /2017 ዓ.ም
