ጄ አር ፔትሮልዬም ፤ ሁለት ነጥብ አምስት ቢሌዬን ብር በላይ ኢንቨስት በማድረግ የዘጠኝ ሚሊዬን ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ ማከማቻ ዲፖን በቦሌ ዓለማቀፍ አየር ማረፊያ ግቢ ውስጥ ገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጓል፡፡
ይህ ግዙፍ የአውሮፕላን ነዳጅ ማከማቻ ዲፖ ጷግሜ 01 ቀን 2017ዓም ፤ የኩባንያው የማኔጅመንት አባላት፣ የኩባንያው አጋር አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይፋ ተደርጓል፡፡
ኩባንያው በአሁኑ ሰዓት እየጨመረ የመጣውን የሀገሪቱን የሀይል ፍላጎት ለማሟላት በዘርፉ ፤ ከሃምሳ ስምንት በላይ ማድያዎችን መገንባቱን ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል፡፡
እንዲሁም ከአንድ መቶ ሃምሳ በላይ የነዳጅ ቦቴዎችን ከአጋር አካላት ጋር በማሰማራት በመላ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡
የውልሰው ገዝሙ
ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም
