ኪም ጆንግ-ኡን የኑክሌር መሣሪያን በተመለከተ እጅ መስጠት የለም ሲሉ ተናገሩ

የሰሜን ኮሪያው መሪ ፒዮንግያንግ የኑክሌር መሣሪያዎቿን መቼም እንደማትተው ማወጃቸውን የሀገሪቱ የመንግሥት የዜና ወኪል የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና ኤጀንሲ (ኬሲኤንኤ) ዘግቧል።

ኪም በኬሲኤንኤ በተላለፈ ንግግራቸው፦ከደቡብ ኮሪያ ጋር የሚደረግ ማንኛውንም አይነት ውይይት እንደማይኖር አስታውቀዋል።

ሰሜን ኮሪያ የመከላከያ ኃይሏን ለማጠናከር አዲስ “ምስጢራዊ መሣሪያ” እንደታጠቀች ተናግረዋል።

የደቡብ ኮርያ ፕሬዝዳንት፤ ሰሜን ኮርያ ያሏትን የኒውክሌር መሳሪያዎች በማስወገድ ፋንታ ተጨማሪ የማምረት ተግባሯን እንድታቆም በዶናልድ ትራምፕ እና ኪም ጆንግ ኡን መካከል የሚደረግ ስምምነትን እንደሚቀበሉ ለቢቢሲ ገልጸው ነበር።

ፕሬዝዳንት ሊ ጄ ምያንግ፤ ሰሜን ኮርያ በዓመት ከ15 እስከ 20 ተጨማሪ የኔውክሌር መሳሪያ እያመረተች እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ተጨማሪ መሳሪያዎችን ማምረት እንድታቆም ማድረግ ሙሉ በሙሉ የኒውክሌር መሳሪያ እንዳይኖራት ከማድረግ አንጻር “ተጨባጭ እና ትክክለኛ ጊዜያዊ የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃ” እንደሆነም ገልጸዋል።

ሰሜን ኮርያ ራሷን የኔውክሌር ኃይል ባለቤት አድርጋ ያቀረበቸው በአውሮፓውያኑ 2022 ሲሆን መሳሪያዎቿን በጭራሽ እንደማታስወግድም ተናግራለች።

መስከረም 12/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *