ጋምቤላ ክልል ለኢንቨስትመንት መሬት ከሰጠኋቸው ባለሃብቶች ውስጥ ወደ ስራ የገቡት ከግማሽ በታች ናቸው አለ

በጋምቤላ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፉ ከ6 መቶ በላይ ባለሃብቶች መሬት ቢወስዱም ወደ ስራ የገቡት ግን 2መቶ80 መሆናቸው ተገልጿል።

መሬት ወስደው ወደ ልማት ባልገቡ ባለሃብቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ያስታወቁት የክልሉ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ሎው ኡቡፕ፤ የማልምት ፍላጎት ወዳላቸው ኢንቨስተሮች መሬት የማሸጋገር ስራ መከናወኑን አንስተዋል።

ኮሚሽነሩ ለኢንቨስትመንት መሠረታዊ የሆነው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ መሆን አስፈላጊ በመሆኑ ይህን ለማረጋገጥ ብዙ መሠራቱን ተናግረዋል።

በክልሉ በዝናብ ሊለማ የሚችለው የእርሻ መሬት ከጠቅላላው የቆዳ ስፋት ውስጥ 16 በመቶ ሲሆን፤ ለዘመናዊ የመስኖ ንግድ እርሻ የሚሆነው ደግሞ 10 በመቶ እንደሆነ ገልፀዋል።

ይህንን ለማልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው ባሮ እና አኮቦን ጨምሮ ግዙፍ ወንዞች መኖራቸውንም አንስተዋል።

አቤል እስጢፋኖስ

መስከረም 12/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *