ነዳጅ ለሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች የሚሰጠው ትኩረት ወደ ዜሮ ወርዷል ሲል የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ

ያሉትን የነዳጅ ተሽከርካሪዎችንም ወደ ኤሌክትሪክ የመቀየር እንዲሁም ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ለመቀየር የተያዘ ስታንዳርድ መጽደቁን እና መመሪያዉ ላይ እየተሰራ እንደሆነም ሰምተናል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን፤ቤንዚልን መጠቀም ከፍተኛ መጠን ያለው ካርቦን ሞኖክሳይድ እና ናይትሮጅን ኦክሳይዶችን እንደሚፈጥር ገልጸዉ ፤ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በስፋት በትራንስፖርት ሲስተም ውስጥ ማስገባት ለእነዚህ ችግሮች መፍትሄ እንደማበጀት ይቆጠራል ብለዋል፡፡

በዚህም አገር ዉስጥ የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ መደረጉንም አንስተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዉ አሁን ነዳጅ ለሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች የሚሰጠዉ ትኩረት ወደ ዜሮ ወርዷል ነው የሚሉት፡፡

ያሉትን የነዳጅ ተሽከርካሪዎችንም ወደ ኤሌክትሪክ የመቀየር፣ እንዲሁም ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ለመቀየር የተያዘ ስታንዳርድ መጽደቁን እና መመሪያ ላይ እየተሰራ እንደሆነም ገልጸዋል።

ነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ፣ እንዲሁም ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ለመቀየር ተነሳሽነት ላላቸው ደግሞ መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

አሁን ላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በቀላሉ እንዲገቡ ሰንሰለቱ ቀላል እንደሚደረግ አንስተዉ፤ ዋነኛዉ መፍትሔ ግን ፋብሪካዎችን ሀገራችን ላይ በመስራት እዚሁ እንዲገጣጠሙ ማድረግ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዉ ከጥቂት አመታት በኋላ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል ባይ ናቸው፡፡

ለዓለም አሰፋ

ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *