በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በተደረገ ቁጥጥር የአካባቢ ጤና አጠባበቅና የምግብ ደህንነት መጓደል ችግር የተኘባቸው 3መቶ23 ተቋማት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡
ግምታዊ ዋጋችው ከ23 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተበላሹና የመጠቀሚያ ግዜ ያለፈባቸው ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች እንዲወገዱ መደረጉንም በባለስልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር እስጢፋኖስ ጌታቸው ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡
ሁለት ተቋማት ከተፈቀደላቸው ስራ ውጭ ሲሰሩ በመገኘታቸው ንግድ ፍቃዳቸው እንዲሰረዝ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም 2መቶ63 ተቋማት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ 35 ተቋማት በጊዚያዊነት እንዲታሸጉ እና 20 ተቋማት ደግሞ በገንዘብ እንዲቀጡ መደረጉን ገልፀዋል፡፡
ተቋማቱ ያለ ጤና ብቃት ማረገጋጫ በመስራት፣ ህገወጥ የምግብ እና የአገልግሎት ጊዜ ያለፈበት ምርት በመያዝ፣ የንጽህና ጉድለት፣ ትንባሆ ክልከላ በመተላለፍ እንዲሁም ከስታንዳርድ በታች አገልግሎት በመስጠት ቅጣት የተጣለባቸው መሆናቸውን ዳይሬክተሩ አንስተዋል፡፡
ሐመረ ፍሬው
ህዳር 01/2018 ዓ.ም
