የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጡን በመሰረታዊነት የሚቀይሩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገለጸ

በቢሮው የደንበኞች መስተንግዶ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዘውዴ እንደተናገሩት፤በግብር ከፋዩ ማህበረሰብ የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመውሰድ ከአመራሩና ከፈፃሚው ጋር ውይይት ተካሂዶባቸዋል ብለዋል።

በዚህም ፍትሀዊ የሆነ የገቢ አሰባሰብ እንዲኖርና በተቋሙ ወጥና ቀልጣፋ የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማስፈን የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።

ከወረዳ አንስቶ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና በዋና ቢሮ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በማዘመን አገልግሎት ለመስጠት የማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛልም ነው ያሉት።

ቢሮው የግብር ከፋዩን ግዜና እንግልት እንዲሁም ተጨማሪ ወጪ ለመቀነስ የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እየተጠቀመ መሆኑን አመላክተዋል።

ግብር ከፋዮች የ2017 ዓመታዊ የግብር ማሳወቂያ ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ግብራቸውን በወቅቱ በመክፈል ከአላስፈላጊ ወለድና ቅጣት ራሳቸውን ሊጠብቁ እንደሚገባም አሳስበዋል።

አቤል እስጢፋኖስ

ህዳር 01/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *