የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፤ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ በ2018 አንደኛ ሩብ ዓመት ላይ ሁለት 2መቶ 29 ተጠርጣሪዎችን እጅ ከፍንጅ መያዛቸዉን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በሩብ ዓመቱ ከባድ ወንጀልን 42 በመቶ መቀነስ መቻሉን ኮማንደር ማርቆስ ገልጸዋል።
በቴክኖሎጂ ዘርፍ በማዕከል ደረጃ ተቋሙንና አካባቢዉን የሚጠብቁ 1መቶ60 ካሜራዎች መገጠማቸዉንና፤ በ11ዱ ክፍለ ከተሞች 1 ሺህ 5መቶ የደህንነት ካሜራዎች መገጠሙን ተናግረዋል።
ቴክኖሎጂን በማዘመን የደህንነት ካሜራዎች መግጠም ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ያለበት ዋነኛ አላማ ፤ በከተማዋ አስተማማኝ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ መሆኑን አስታዉቀዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ህዳር 01/2018 ዓ.ም
