በዩክሬን ውስጥ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር አወዛጋቢ መግለጫ ሰጥቷል።
ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ዶኔትስክ ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ወሳኝ ከተማ ፖክሮቭስክን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሯን ዛሬ አስታውቃለች።
ፓክሮቭስክ ለዩክሬን ጦር ኃይሎች በምስራቃዊው ግንባር ላይ የጦር መሳሪያዎችን እና ሌሎች አቅርቦቶችን ለማጓጓዝ ቁልፍ የነበረች፣ የመንገድና የባቡር መስመር መገናኛ ማዕከል ናት ።
ከተማዋ በሩሲያ ሙሉ የዶኔትስክን ግዛት ለመቆጣጠር በምታደርገው ጥረት እንደ “መግቢያ በር” ተደርጋ መታየቶንና ሩሲያ ከተማዋን መያዟ በምስራቃዊው ግንባር ለኪየቭ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ሽንፈት ሊሆን ይችላል ተብሎ ይገመታል።
ዩክሬን እስካሁን በጉዳዮ ላይ ምንም ምላሽ አልሰጠችም ተብሏል።
ይሁን እንጂ፣ የዩክሬን ባለሥልጣናት በቅርብ ቀናት ውስጥ በፖክሮቭስክ ዙሪያ ያለው ሁኔታ “በጣም አስቸጋሪ” እንደሆነ እና ሩሲያ ከፍተኛ ጥቃት እየሰነዘረች እንደሆነ ሲገልጹ ቆይተዋል ሲል አልጀዝራ ዘግቧል
ሱፊያን አህመድ
ህዳር 23/2018 ዓ.ም
