በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ እያጠናከርን ነው አሉ የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ከኢትዮጲያው አቻቸው ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ጋር ጋር በስልክ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ በ2027 COP32 የአየር ንብረት ኮንፈረንስን እንድታዘጋጅ በመመረጧ እንኳን ደስ ያለህ ብየዋለሁ ያሉት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ሳር፡፡

በተጨማሪም የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን አስመልቶ በመከላከያ፣ በፖሊስ፣ በፈጠራ፣ በልማት እና በሌሎች በጋራ በምንሰራባቸው ዘርፎች ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ እያጠናከርን ነው ማለታቸውን ከእስራኤል ኤንባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ህዳር 23/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *