መቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና አረጋዊያን መርጃ ማዕከል በየቀኑ 3 ሚሊዮን ብር ለማውጣት በመገደዱ፣ ያስጀመረው ሆስፒታል ባለመጠናቀቁ፣ በየክልል ከተሞች አዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈቱ ለጋሽ እጆች የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉለት ጠይቋል።
ዛሬ ባካሄደው የውይይትና የምስጋና ፕግራም፣ ባለፈው አመት በርካቶች እንደተረባረቡበት አይነት በቀጥታ ስርጭት ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ የፊታችን የካቲት 1 2018 ዓ/ም እንደሚካሄድ ገልጿል።
እስከዚያው ሁሉም መረጃውን በማዳረስ፣ መረጃውን የሚሰሙ ከወዲሁ ተዘጋጅተው የአቅማቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ማዕከሉ ጥሪ አቅርቧል።
የካቲት 1/2018 ዓ/ም ገቢ የማሰባሰብ ሥራ ከባለፈው አመት የሚለየው በአሁኑ በመቄዶንያና በማንኛውም የግለሰቦች ዩቱብ በቀጥታ ስለሚተላለፍ መሆኑን የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ገልጸዋል።
ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም
