የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ ከቱርክ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ አቻዎቻቸው ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ እርምጃውን ባወጡት መግለጫ ኮንነዋል፡፡
በሌላ በኩል የአፍሪካ ህብረት እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን እውቅናን ውድቅ አድርጓል ።
የአፍሪካ ህብረት ለሶማሊያ አንድነት እና ሉዓላዊነት ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት አለው ብሏል ባወጣው መግለጫ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ያሳለፉት ይህ ውሳኔ ቴላቪቭ ለምስራቅ አፍሪካዊቷ የሶማሊላንድ ግዛት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያው ሀገር አድርጓታል፡፡
ሶማሊላንድ ከ1991 ጀምሮ የራሷ መንግሥት፣ የምርጫ ስርዓት እና ተቋማት ያሏት ራሷን የምታስተዳድር ግዛት ብትሆንም፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እውቅና ያልተሰጣት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አካል ተደርጋ ትቆጠራለች።
ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም
