በአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ 52 ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በህገ-ወጥ ተግባር እና በብልሹ አሰራር ላይ ተሰማርተው ባገኛቸው ሃምሳ ሁለት ሰራተኞች ላይ ጥብቅ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

ኤጀንሲው ይህንን እርምጃ ይፋ ያደረገው፤የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በሁሉም የከተማዋ ወረዳዎች ማዳረሱን በገለጸበት የስድስት ወራት የሪፖርት ግምገማው ላይ ነው።

ኤጀንሲው የአገልግሎት አሰጣጥ ግልጽነትን ለማረጋገጥ ባደረገው ጥብቅ ክትትል፤ በከባድ እና በቀላል የዲሲፕሊን ጉድለት ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ሰራተኞችን ለይቷል።

በዚሁ መሠረት፤በድምሩ በሃምሳ ሁለት ሰራተኞች ላይ የቅጣት እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፤ከእነዚህም መካከል አስራ አምስቱ በፈጸሙት ከባድ ጥፋት ጉዳያቸው በህግ ተይዞ በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።
በተጨማሪም ሁለት ሰራተኞች ከስራ ሙሉ በሙሉ እንዲሰናበቱ ተደርጓል።

ልዑል ወልዴ

ጥር 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *